ቃታር ኢራን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ለዛቻ እንዳትጠቀም አሳሰበች

የቃታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒ፤ ኢራን ስትራቴጂካዊ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን የገልፍ አገራትን “ለማስፈራሪያ” ወይም “ለጥቁር ድርድር” (blackmail) ልትጠቀምበት አይገባም ሲሉ አሳሰቡ።

ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ ንግድና ለነዳጅ ልውውጥ ያለውን ወሳኝነት በመጥቀስ፣ መተላለፊያው ከፖለቲካዊ ውጥረቶች ነፃ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

ቃታር በቀጠናው ያለውን አለመረጋጋት ለመቅረፍ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እያደረገች መሆኑን የገለጹት ሼክ መሐመድ፣ ማንኛውም በባህር ወሽመጡ ላይ የሚደረግ የጉልበት እርምጃ ወይም ዛቻ በቀጠናው ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋ እንደሚደቅን አስገንዝበዋል።

ይህ የቃታር መግለጫ የተሰማው፣ በኢራን እና በአንዳንድ የገልፍ አገራት እንዲሁም በምዕራባውያን መካከል ያለው ውጥረት በጨመረበት እና መተላለፊያውን አስመልክቶ የተለያዩ ስጋቶች እየተደመጡ ባሉበት ወቅት ነው።

የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በዓለም ላይ ካለው የነዳጅ ንግድ ውስጥ ሲሶው የሚተላለፍበት ወሳኝ የውሃ መስመር መሆኑ ይታወቃል።

ልዑል ወልዴ

ግንቦት 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *