የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የሀገራቸውና የአሜሪካ ግንኙነት ስላለው እምቅ አቅም መልካም ነገሮች ቢወሩም፣ በተጨባጭ ግን “ምንም የተከናወነ ነገር የለም” ብለዋል ።
ላቭሮቭ በቴክኖሎጂና በኢነርጂ ዙሪያ የተነገሩ “መልካም ቃላት” ፍሬ አላፈሩም ቢሉም፣ ትራምፕ ውይይት መጀመራቸውን ግን ሞስኮ እንደምታደንቅ ገልጸዋል።
ከ2004 ጀምሮ ሚኒስትር የሆኑት ላቭሮቭ ለአርቲ ኢንዲያ እንደተናገሩት የአሁኑ ውይይት በጆ ባይደን ዘመን ከነበረው አይለይም፤ከመደበኛ ንግግር ውጭ፣ ሌላው ነገር ሁሉ ባይደን የጀመሩትን መዋቅር የተከተለ ነውም” ብለዋል።
በተጨማሪም በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን የተጣሉት ማዕቀቦች መቆየታቸውንና የትራምፕ አስተዳደርም የሩሲያን ኢኮኖሚ ለመቅጣት የራሱን አዳዲስ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ በኋላ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ውይይት ቢጀምሩም፣ በዩክሬን ጦርነትን ለማቆም የገቡት ቃል ግን እስካሁን አልተሳካም።
ሳራ ዮሐንስ
ግንቦት 05/2018 ዓ.ም
