ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ዠንግ ትራምፕ ከኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ሲወርዱ ለመቀበል በአውሮፕላን ማረፊያው ተገኝተዋል።
ሃን ከቻይና ከፍተኛ መሪዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ትራምፕን እሳቸው እንዲቀበሉ መላኩ ቤጂንግ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ያላትን አክብሮት እንደማሳየት ተቆጥሯል።
ትራምፕ በ2017 ጉብኝታቸው ወቅት፣ ቻይና የላከችው ዝቅተኛ ማዕረግ ያላቸውን የመንግስት አማካሪ ያንግ ጄቺን ነበር። ሃን ባለፈው ዓመት በተካሄደው የትራምፕ በዓለ ሲመት ላይም ተገኝተው ነበር።
ሮይተርስ እንዳለው ትራምፕ በደመቀ አቀባበል ነው ቤጂንግ የገቡት፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ከቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር ውይይት ለማድረግ ነው ቤጂንግ፣ ቻይና የደረሱት ።
ፕሬዝዳንቱ ወደ ፕሬዝዳንታዊ ተሽከርካሪያቸው ሲገቡ በባንድ ሙዚቃ እና ባንዲራ እያውለበለቡ በሚዘምሩ ሰዎች ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በትራምፕ ልዑክ ውስጥ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች የተካተቱ ሲሆን፣ የቴስላው ባለቤት ኤሎን ማስክም በአውሮፕላን ማረፊያው ታይቷል።
ግንቦት 05/2018 ዓ.ም
