በህንድ በደረሰ ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ 90 የሚጠጉ ሰዎች ህይወት አለፈ

በህንድ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚ በሆነችው ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በጣለው ኃይለኛ ዝናብ እና በረዶ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ የ90 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

የግዛቲቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለጹት፤ አውሎ ንፋሱ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

በከባድ ዝናቡና በረዶው ሳቢያም የሰው ህይወት ከማለፉ ባለፈ በንብረት ላይም የከፋ ጉዳት ደርሷል።

የነፍስ አድን ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ የተጎጂዎች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል።

ልዑል ወልዴ

ግንቦት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *