የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በዓለም ላይ እጅግ አስፈላጊው ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ዢ ገለጹ


የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በዓለም ላይ እጅግ አስፈላጊው የሁለትዮሽ ግንኙነት መሆኑን ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ተናገሩ።
 
ይህ ግንኙነት የ1.7 ቢሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆኑትን የሁለቱን ሀገራት ደህንነት ብቻ ሳይሆን፣ ከ8 ቢሊዮን በላይ የሚሆነውን የዓለም ህዝብ ጥቅም የሚነካ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
 
‘አሜሪካን ዳግም ታላቅ ማድረግ’ ከቻይና እድገት ጋር አብሮ ይሄዳል ብለዋል ዢ ፡፡
 
ጉብኝቱን “ታሪካዊ” ሲሉ የጠሩት ዢ፣ “የቻይና ብሔራዊ ተሃድሶ” እና “አሜሪካን ዳግም ታላቅ ማድረግ” የሚሉት ግቦች ጎን ለጎን ሊራመዱ የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
 
የቻይናው ፕሬዝዳንት ለሁለቱ ሀገራት እድገትና መጻኢ እድል መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ንግግራቸውን አጠናቀዋል። ብርጭቆቸውን ወደ ላይ ከፍ በማድረግም “ለጤናችን!” ብለዋል።
 
ቀጥለው ንግግር ያደረጉት ትራምፕ ስብሰባውን ‘ታላቅ ክብር’ ሲሉ ገልጸውታል፡፡
 
ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት መግለጫ፣ “ከሌላው የተለየና እጅግ ድንቅ አቀባበል” እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።
 
ዛሬ ቀደም ብሎ ከፕሬዝዳንት ዢ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንና በርካታ ጉዳዮችን ለመወያየት “ውድ” እድል ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
 
“ከእርስዎ ጋር መሆን ትልቅ ክብር ነበር” ሲሉም ለፕሬዝዳንት ዢ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል ያለው ቢቢሲ ነው።
 
ግንቦት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *