የዩጋንዳ ባለስልጣናት እንደገለጹት የዓለም ጤና ድርጅት የኢቦላ ስርጭትን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ በሰጠበት ወቅት ፤ ከ100 በላይ ሰዎች በለይቶ ማቆያ (ኳራንቲን) ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርጓል ብለዋል።
ባለስልጣናቱ ሁኔታው በቁጥጥር ስር መሆኑን አጥብቀው የገለጹ ሲሆን፤ዩጋንዳ የቀድሞ ወረርሽኞችን በመቆጣጠር ረገድ ያላት ልምድ የምላሽ አሰጣጥ አቅሟን እንዳጠናከረው ተናግረዋል።
ዩጋንዳ ቀደም ሲል የኢቦላ፣ የኮቪድ-19 እና የኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽኞችን በብቃት መቆጣጠሯን አክለው ገልጸው፣ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና የጤና መመሪያዎችን እንዲከተል አሳስበዋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው የዓለም ጤና ድርጅት በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እየተባባሰ የመጣውን የኢቦላ ወረርሽኝ ‹‹መጠንና ፍጥነት›› በተመለከተ ማስጠንቀቂያ በሰጠበት ወቅት ነው።
በኮንጎ የሚገኙ ባለስልጣናት ቢያንስ 1መቶ31 ሰዎች መሞታቸውንና ከ5መቶ በላይ ተጠርጣሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸው፣ ይህም ቫይረሱ በክልሉ ውስጥ የበለጠ ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
እስከዳር ግርማ
ግንቦት 12/2018 ዓ.ም
