የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኢድ-አል አድሀ (አረፋ) በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት1447ኛውን የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል አስመልክቶ በበዓሉ ሰሞን የሚኖረውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ለማስተናገድና መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወኑን አስታውቋል።

ተቋሙ ባደረገው አጠቃላይ የቅድመ መከላከል ፍተሻ ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑት ችግሮች መካከል በዋናው ኔትዎርክ 80 በመቶ እንዲሁም በትራንስፎርመር ላይ 70 በመቶ የሚሆኑትን መቅረፍ መቻሉን ጠቅሷል፡፡

​እንዲሁም የመሠረተ-ልማት ማሻሻያ እና የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ ስራዎችን ያከናወነው ተቋሙ፥ በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት ለሚከሰቱ ድንገተኛ ብልሽቶች አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ሃይል በሁሉም አደረጃጀቶቹ ማዋቀሩን ገልጿል፡፡

​በበዓሉ ዕለትም በተመረጡ ማዕከላት የካርድ መሙላት አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች የኃይል እጥረት እንዳይገጥማቸው ካርዳቸውን አስቀድመው እንዲሞሉ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *