ተቋሙ 4መቶ12 ሺህ 5መቶ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 88 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል።
ከተሰበሰበው ደም ውስጥ 99 ነጥብ 7 በመቶው ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች የተገኘ ሲሆን፥ ከባለፈው ዓመት አንጻር 18 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።
በተጨማሪም 55 ሺህ 2መቶ19 ዩኒት ደም ወደ ደም ተዋፅኦ መቀየሩን እና በሀገር አቀፍ ደረጃ 85 በመቶ የጤና ተቋማት የደም ፍላጎት መሟላቱን አስታውቋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
