ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) የአፍሪካ ቀን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት” 63 ዓመታት በፊት አባቶቻችን እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው ነፃ እና የተባበረች አፍሪካን አልመው ነበር፤ ያ ህልም ዛሬም እንደደመቀ ነው።” ብለዋል፡፡
“ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ኩሩ መኖሪያ እንደመሆኗ መጠን በዚያው የአንድነት መንፈስ ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ጋር አብራ ትቆማለች። ስራው ገና ብዙ ይቀረዋል። ከቃል ወደ ተግባር፣ ከቃል ኪዳን ወደ እድገት እንሻገር” ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሲያክሉም “የአፍሪካ ትልቁ ሀብት ሁል ጊዜም ህዝቦቿ ናቸው፤ በጋራም ወደ ላይ እንመጥቃለን!” ሲሉ ጽኑ ዕምነት እና ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
መልካም የአፍሪካ ቀን ለሁሉም አፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን! አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )
