እርግቦችን ለማባረር በራሱ የሚሰራ የውሃ መርጫ የሰራው ግለሰብ

አንድ ሰው በበረንዳው ላይ በሚያርፉ እና በሚጸዳዱ እርግቦች በመማረሩ፣ ወፎቹን ለይቶ በማወቅ ውሃ የሚረጭ ራሱን የቻለ የውሃ ሽጉጥ ሰርቷል።

ይህንን ፈጠራ ለመስራትም በባትሪ የሚሰራ የውሃ ሽጉጥ፣ አነስተኛ ኮምፒውተር፣ ካሜራ፣ የዕቃ መለያ የኤአይ ሶፍትዌር፣ ሁለት ትናንሽ ሞተሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ተጠቅሟል።

የውሃ ሽጉጥ አሰራር ቀላል ነው፤ እርግብ ወደ በረንዳው ስትጠጋ ካሜራው ያያታል፤ በመቀጠልም የኤአይ ሶፍትዌሩ እርግብ መሆኗን ካረጋገጠ በኋላ ሞተሮቹ ሽጉጡን ወደ ወፏ አቅጣጫ አዙረው ውሃ በመርጨት ያባርሯታል።

የዚህ ፈጠራ ቪዲዮ በኢንተርኔት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ ብዙ ሰዎች የውሃ ሽጉጡ ለገበያ ቢቀርብ ወዲያውኑ እንደሚገዙት ገልጸዋል።

አንዳንዶች ደግሞ ድመቶች በጓሯቸው ላይ እንዳይጸዳዱ ለመከላከል ተመሳሳይ መፍትሄ ለማዘጋጀት አስበው እንደነበር ተናግረዋል።

ፈጣሪው የውሃ ሽጉጡን የመሸጥ እቅድ ባይኖረውም ሶፍትዌሩን ሌሎች እንስሳትን ወይም ሰዎችን ጭምር ለይቶ እንዲያባርር አድርጎ ማስተካከል እንደሚቻልም ተናግሯል፡፡

ሐመረ ፍሬዉ

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *