የአሜሪካእናኢራንየሰላምስምምነትተስፋ ቢጣልበትም ፤የእስራኤልጦርበሊባኖስለረጅምጊዜለመቆየትእየተዘጋጀመሆኑተገለጸ

የእስራኤል ጦር  ባለብዙ ግንባር ጦርነቶችን ያቆመው የአሜሪካ እና የኢራን ስምምነት ቢኖርም በሊባኖስ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለሚቆይ ወረራ መዘጋጀቱን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን  ስማቸው ያልተጠቀሰ የእስራኤል የደኅንነት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው  ጦሩ በሊባኖስ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ዝግጁ ነው።

በተጨማሪም ዋሽንግተን  እና ቴህራን በስዊዘርላንድ ዓርብ ዕለት ስምምነቱን ለመፈረም እየተቃረቡ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ሰራዊቱ “በሊባኖስ ውስጥ ለሚፈጠሩ ለማንኛውም ዓይነት ሁነቶች” ዝግጁ መሆኑ ተገልፁዋል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ  የተኩስ አቁም ስምምነት ቢኖርም እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የምታደርገው ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ቀደም ሲል ማክሰኞ ዕለት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በሊባኖስ ያለውን ጦርነት ማቆም ከዋሽንግተን ጋር ለሚደረገው ስምምነት “ዋነኛ አካል” መሆኑን እና የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ግዛት መውጣቱንም እንደሚያካትት ተናግረው ነበር።

ሀና ሰይፉ

ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *