በሊባኖስ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በትራምፕ እና በኔታንያሁ መካከል አለመግባባት መንገሡ ተሰምቷል

የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ አራት ሰዎችን መግደሉን ተከትሎ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኔታንያሁ በሊባኖስ ጉዳይ ላይ “ኃላፊነት ሊሰማቸው ይገባል” ብለዋል። ድርጊቱን ተከትሎም የአሜሪካ ኮንግረስ ለእስራኤል ባለው ድጋፍ ዙሪያ አዲስ መከፋፈሎች መታየታቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ኢራን በበኩሏ፤ በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል የመግባቢያ ስምምነት ከተደረገ ወዲህ እስራኤል በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት 84 ጊዜ ጥሳለች ስትል ከሳለች። ጥቃቶቹ የሚቀጥሉ ከሆነም “ጠንካራ እርምጃ” እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

በክልሉ ባለው ሌላ ውጥረት፣ የኢራን ድፍድፍ ዘይት የጫነች ሦስተኛ መርከብ በአሜሪካ ባህር ኃይል የተጣለውን የእገዳ መስመር በመጣስ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ ተጉዛለች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ማንኛውም ስምምነት፤ የታገዱ የኢራን ንብረቶች እንዲለቀቁ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀቦች እንዲነሱ እና እስራኤል ከሊባኖስ ሙሉ በሙሉ እንድትወጣ የሚያስገድድ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ሜሮን ገብሬ

ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *