ዋሽንግተን እና ቴህራን የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረሙ

አሜሪካ እና ኢራን ለወራት የዘለቀውን ግጭት ለማቆም የሚያስችል የ60 ቀናት ጊዜያዊ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን ተከትሎ አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ ጥላው የነበረውን የባህር ላይ እገዳ ያነሳች ቢሆንም፤ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በፈጸመችው እና የሶስት ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የአየር ድብደባ ምክንያት የምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ የጄኔቫ የሰላም ድርድር ጉዞ በመጨረሻው ሰዓት ተሰርዟል።

የኢራን ተደራዳሪዎችም ወደ ስዊዘርላንድ ከመጓዛቸው በፊት ሊባኖስን የሚያካትተው ይህ የተኩስ አቁም በተግባር መዋሉን ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስምምነቱ በሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ አስነስቷል።

በኢራን በኩል ከፍተኛ ባለስልጣናት የሀገሪቱን ‹‹ድል›› እያበሰሩ አሜሪካ ውሉን ከጣሰች አስደንጋጭ ምላሽ እንደሚሰጡ ሲያስጠነቀወቁ፤በአሜሪካ ደግሞ የዲሞክራቲክ ሴኔት መሪ ቹክ ሹመር እና የሪፐብሊካን ጥንካሬ አቋም አራማጆች በትራምፕ አስተዳደር ላይ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።

ተቺዎች ስምምነቱ ለኢራን የነዳጅ ማዕቀብ እፎይታ እና 3መቶ ቢሊየን ዶላር ለመልሶ ግንባታ ይሰጣል ቢሉም፤ ጄዲ ቫንስ ግን ‹‹አንድ ሳንቲም የአሜሪካ ገንዘብ ወደ ኢራን አይሄድም›› በማለት ስምምነቱን ተከላክለዋል።

ዋሽንግተን እስራኤልም ወታደራዊ ዘመቻዋን እንድታቆምና የስምምነቱን ውል እንድታከብር ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፋለች ሲል አልጄዚራ ዘግቧል።

ሳራ ዮሐንስ

ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *