የሩሲያ ወታደሮች መከማቸት የዩክሬንን ዶንባስ ቀጣና ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ቁልፍ መግቢያ ተደርጋ የምትወሰደውን የኮስታንቲኒቭካ ከተማን አደጋ ላይ ጥሏታል ተብሏል።
ከተማዋ አሁን ላይ በማንም ቁጥጥር ስር ወደማትገኝበት ቀጣና የተቀየረች ሲሆን፥ የሩሲያ ኃይሎች በከተማዋ ሰሜናዊ ዳርቻዎች ጭምር ታይተዋል ነዉ የተባለዉ።
ሞስኮ የዩክሬን ጦር ክፍሎችን መክበቧን ብትገልጽም ኪቭ ግን ይህንን አስተባብላለች።
የዩክሬን ድሮን አብራሪዎች እና መኮንኖች የሩሲያ ወታደሮች በህንፃዎች እና በዛፎች እየተሸሸጉ በዝግታም ቢሆን ወደ ከተማዋ እየገቡ መሆናቸውን እና የዩክሬን የድሮን ጣቢያዎችን በከባድ መሳሪያዎች በማጥቃት የመከላከል አቅማቸውን እያዳከሙ መሆኑን አምነዋል።
ይህ የሩሲያ ግስጋሴ ዩክሬን በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች እና በክሬሚያ የአቅርቦት መስመሮች ላይ ካደረሰችው ጥቃት ትኩረትን እያዞረ ይገኛል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሳራ ዮሐንስ
ሰኔ 15/2018 ዓ.ም
