በአረጋውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በዝምታ ማለፍ እንደማይገባ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአረጋውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ህብረተሰቡና የሚዲያ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

ኮሚሽኑ አረጋውያን በቤተሰብ፣ በአካባቢ ነዋሪዎችና በተለያዩ አካላት አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው፣ ንብረታቸው እንደሚዘረፍና ከመኖሪያ ቤታቸው እንደሚፈናቀሉ ገልጿል።

የኮሚሽኑ ተወካይ እንደገለጹት፤ ህብረተሰቡ በአረጋውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ‹‹ነውር ነው›› በሚል በመደበቅ ለተጨማሪ ጥቃት ማጋለጥ የለበትም።

ማንኛውም ጥቃት ሲፈጸም በነጻ ስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል ሪፖርት እንዲደረግ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የሚዲያ አካላት የአረጋውያንን ጉዳይ በአመት አንድ ቀን ብቻ ከማስታወስ ባለፈ ተከታታይነት ያለው ዘገባ በመስራት ችግሩን ለማቃለል እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *