ገዢው በቴሌግራም ባወጡት መግለጫ፥ በጥቃቱ ሳቢያ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውን እና በከተማዋ ከሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በአንዱ ላይ የኢንዱስትሪ ተቋማት መጎዳታቸውን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የበርካታ አፓርታማ ህንጻዎች የውጭ ገጽታዎችና መስኮቶች እንዲሁም በርካታ ተሽከርካሪዎች መጎዳታቸውን አክለዋል።
ገዢው ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኙ ሲሆን፥ ለቆሰሉት ደግሞ ፈጣን ማገገምን ተመኝተዋል።
ገዢው በክልሉ ተደቅኖ የነበረው የሚሳኤል ስጋት ማስጠንቀቂያ መነሳቱን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፥ ከጥቃቱ በኋላ የተከሰቱትን ሁኔታዎች የሚያሳዩ ፎቶዎችን ወይም ቪዲዮዎችን በተለይም ያሉበትን ቦታ ሊያጋልጡ የሚችሉ ምስሎችን በኢንተርኔት ላይ ከመልቀቅ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።
ሀና ሰይፉ
ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
