የኢራን ዋና ተደራዳሪ እና መሀመድ ባጋር ጋሊባፍ ከአሜሪካ ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት 12 ቢሊየን ዶላር የታገደ የኢራን ገንዘብ እንደሚለቀቅ አስታወቁ።
ይህ የሆነው አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለቻቸውን አንዳንድ ማዕቀቦች ለጊዜው በማለስለስ ኢራን ዘይትና ፔትሮኬሚካል ምርቶችን እስከ ኦገስት 21 ድረስ እንድትሸጥ ከፈቀደች በኋላ ነው።
በሌላ በኩል የሄዝቦላህ የፖለቲካ ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ማህሙድ ቃማቲ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከጣሰች በተመሳሳይ ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠንቅቀዋል።
ቃማቲ ሄዝቦላህ በሙሉ ዝግጁነት ላይ ነው ማንኛውንም ጥሰት ለመመከት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።
ትዕግስት ግርማ
ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
