በአሜሪካ እና በኢራን ጥቃት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ጨመረ

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ0.9 በመቶ በማደግ በአንድ በርሜል 73.21 ዶላር ደርሷል ተባለ።

ይህ የዋጋ ጭማሪ የመጣው በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረጉት የእርስ በእርስ ጥቃቶች በሆርሙዝ የባህር መስመር ላይ መደበኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በፍጥነት ይመለሳል የሚለውን ተስፋ ስላደበዘዙት ነው ተብሏል።

በዚሁ ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ቀደም ሲል የነበረውን የሰላም ተስፋ በማጣት የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

በሌላ በኩል በእስያ የቴክኖሎጂ ገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ ታይቷል።

በተለይም በጃፓን እና በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ የኤአይ እና የሰሚኮንዳክተር ቺፕ አምራች ኩባንያዎች እንደ ሳምሰንግ፣ ኤስኬ ሃይኒክስ እና ሶፍትባንክ ያሉ ከፍተኛ የትርፍ ሽያጭ እና የወደፊት እጣ ፈንታ ስጋት በመፈጠሩ የአክሲዮን ዋጋቸው ቀንሷል።

በአንጻሩ የሆንግ ኮንግ እና የታይዋን ገበያዎች መጠነኛ ዕድገት አሳይተዋል ተብሏል።

ምንም እንኳን ውጥረቱ ቢቀጥልም፤ ሁለቱ ሀገራት ግጭቱን ለማቆም እና የጀመሩትን የሰላም ስምምነት ለማስቀጠል በኳታር ዶሃ ላይ ማክሰኞ ዕለት ውይይት ለማድረግ መስማማታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልጸዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ሳራ ዮሐንስ

ሰኔ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *