አሜሪካ እና ኢራን በሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ ጉዳይ ለመወያየት ተስማሙ

አሜሪካ እና ኢራን በቅርቡ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ለማቆም በመስማማት በሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ ዙሪያ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት ማክሰኞ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ለመገናኘት መስማማታቸውን አክሲዮስ የዜና ተቋም ዘግቧል።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ የኢራን መሆኑን ገልጸው፤ ቴህራን ከምትመርጠው የመርከብ መተላለፊያ መንገድ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ውጥረትንና ግጭትን ያባብሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል የሊባኖስ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ናቢህ ቤሪ፤ ቤሩት ከእስራኤል ጋር የተፈራረመችዉ የማዕቀፍ ስምምነት አይጸድቅም ተግባራዊም አይሆንም ብለው ተናግረዋል።

ምክንያታቸውም ስምምነቱ የሊባኖስን መብቶች በበቂ ሁኔታ አያስጠብቅም የሚል ነው።

በጋዛ ሰርጥ ደግሞ የእስራኤል ጦር ኃይሎች አራት ፍልስጤማውያንን መግደላቸው ተዘግቧል።

በተመሳሳይ ሶሪያ እስራኤል የፈጸመችውን ወታደራዊ ጥቃት በማውገዝ ቀጣይ ጥቃቶች በቀጣናው ውስጥ የበለጠ ውጥረትና ግጭት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቃለች።

ትዕግስት ግርማ

ሰኔ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *