በዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከፍ ያለ ውጤት ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል አሉ ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የተፈጥሮ ሳይንስ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች በኦንላይን ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

በዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከፍ ያለ ውጤት ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፡፡

በአዲስ አበባ 131 የፈተና ጣቢያወች ያሉ ሲሆን ፈተናው በበይነ መረብ ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በስድስት ዙር ይሰጣል።

የወረቀት ተፈታኞች ከሃምሌ አንድ ጀምሮ ፈተና መውሰድ እንደሚጀምሩ የተገለጸ ሲሆን ዘንድሮ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በማስጀመርያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት፣ ለፈተናው የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ በርካታ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት የተሻለ ውጤት ይጠበቃል ብለዋል።

ተማሪዎች በራሳቸው፣ በብቃት በልበ ሙሉነት ተፈትነው ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ መልእክት አስተላልፈዋል።

ባለፈው ዓመት 20 በመቶ ብቻ በበይነ መረብ እንደተሰጠ አስታውሰው ዘንድሮ 62 በመቶ በበይነ መረብ ፈተናውን መስጠት እንደተቻለ አንስተዋል፡፡

በቀጣይ ዓመት ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት መታቀዱምን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ እንደ አዲስ አበባ 58 ሺህ 309 ተማሪዎች በ131 የፈተና ጣቢያወች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

በፈተና ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *