“ተማሪዎችን ወደ ‘ዲጂታል ፈጣሪነት’ ለመቀየር ታስቦ ሲሰጥ የቆየው የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ። 


ስልጠናው ታዳጊዎች የነገውን የቴክኖሎጂ ዓለም በባለቤትነት እንዲመሩ መሰረት የጣለ መሆኑ ተመልክቷል።
 
መልቲቾይስ ኢትዮጵያ (MultiChoice Ethiopia) ከ”የኔታ ኮድ” (Yenetta Code) ጋር በመተባበር ለ25 ከፍተኛ አቅም ያላቸው የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየውን የ12 ሳምንታት ጥብቅ የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና በስኬት አጠናቆ አስመርቋል።
 
ጾታዊ ስብጥርን ባማከለ መልኩ (50% ሴት ተማሪዎችን በማሳተፍ) ሙሉ ወጪው ተሸፍኖ የተሰጠው ይህ የSTEM ፕሮግራም፤ ተማሪዎቹ በኮዲንግ፣ በዌብ ሳይት ልማት እና በሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) የታገዘ መሐንዲስነት ላይ ያተኮረ እውቀት እንዲቀስሙ አድርጓል።
 
ተማሪዎቹ በHTML, CSS እና JavaScript በመታገዝ ውስብስብ የሆኑ የዌብ መተግበሪያዎችን ከመሠረቱ እራሳቸው መገንባት ችለዋል ተብሏል።
 
በሥልጠናው ወቅት ተማሪዎቹ ኮዶችን ለመፈተሽና አመክንዮዎችን ለመረዳት የAI መሣሪያዎችን እንደ ረዳት አስተማሪነት መጠቀማቸው ሲጠቀስ ከቴክኒክ እውቀቱ ጎን ለጎን የቡድን ሥራ፣ የትችት አስተሳሰብ (critical thinking) እና የኮሚኒኬሽን ክህሎታቸውን ማሳደጋቸው ተነግሯል፡፡
 
በሥልጠናው ላቅ ያለ ውጤት ላሳዩ ተማሪዎች ልዩ ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን፣ ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የላቀ የSTEM የበጋ ካምፕ (summer camp) ሥልጠና ዕድል ተመቻችቶላቸዋል ሲል በላከልን መግለጫ ገልጻል።
 
“እነዚህ ብሩህ ተማሪዎች ከመሠረቱ የገነቧቸውን ዘመናዊ የዲጂታል መድረኮች በራስ መተማመን ሲያቀርቡ ማየት ትልቅ ኩራት ነው። ወጣቶቻችን አሁን የቴክኖሎጂ ታዛቢዎች አይደሉም፤ በዓለም አቀፉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ የቴክኖሎጂው ፈጣሪዎች ናቸው።” ብለዋል ገሊላ ገብረሚካኤል የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ፡፡
 
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አያልነህ ለማ በበኩላቸው”የሰውን ኃይል ማልማት የሀገራችን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፍጹም መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ አጀንዳን ለማሳካት የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ትብብር ወሳኝ በመሆኑ፣ መልቲቾይስ እና የኔታ ኮድ የዲጂታል ክፍተቱን ለማጥበብ ላደረጉት ጥረት ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።”
 
ይህ ተነሳሽነት መልቲቾይስ አፍሪካ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና የወደፊት የፈጠራ ባለሙያዎችን ለማፍራት ካላቸው ሰፊ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶች መካከል አንዱ ነው።
 
ሰኔ 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *