ሩሲያ የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላን በመጠቀም በዪክሬን ዋና ከተማ በኪየቭ  ላይ በፈጸመችው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ ።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ለ ትልቅ ጥቃት እየተዘጋጀች መሆኗን ካስጠነቀቁ ከሰዓታት በኋላ በከተማው ውስጥ ያሉ ሕንፃዎችን እና በርካታ ሰፈሮች ፈርሰዋል ።

የኪየቭ ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት ቲሙር ተካቼንኮ እንደገለጹት ከሞቱ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት ይገኙበታል ብለዋል።

የዩክሬን አየር ሃይል በበኩሉ ሩሲያ 74 ሚሳኤሎችን እና 496 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በዋነኛነት በመዲናዋ ላይ ማስወንጨፏን አስታውቋል።

የሀገሪቱ መከላከያ ሃይል ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹን መመከት ሲችል 25 የባለስቲክ ሚሳኤሎች እና 12 ሰው አልባ አውሮፕላኖች አና 33 ቦታዎችን መትተዋል።

በከተማዋ በርካታ የእሳት ቃጠሎዎች የተከሰቱ ሲሆን በከተማው በሚገኝ የአምቡላንስ ጣቢያ ላይ ጉዳት መድረሱን እና ይህም ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል ።

የሀገሪቱ የድንገተኛ አደጋ መከላከል አገልግሎት 13 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ30 በላይ ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሲቢሃ የዩክሬን አጋሮች ተጨማሪ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን እንዲልኩ ጠይቀው ሀገሪቱ የሩሲያ ሽብርን ለማስቆም የውግዘት ቃላት ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ እርምጃ ያስፈልጋታል ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ገልጿል ።

ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፣ እራሱን እና ልጆቹንም እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

ሰላማዊት ዲታ

ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *