ናይጀሪያ  ዜጎቼ  ላጡት ንብረት ካሳ እፈልጋለሁ አለች

ናይጄሪያ ሕገ ወጥ ስደተኞችን ያነጣጠሩ የቅርብ ጊዜ ተቃውሞዎችን ተከትሎ አገሪቱን ለቀው ለወጡ ዜጎቿ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ካሳ እንደምትጠይቅ  አስታውቃለች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኪሚኢቢ ኢሞሞቲሚ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፥ ይህ ጉዳይ በሁለቱ መንግሥታት መካከል በከፍተኛ ደረጃ ውይይት ይደረግበታል ብለዋል።

በደቡብ አፍሪካ የናይጄሪያ ጊዜያዊ ከፍተኛ ኮሚሽነር አሌክሳንደር አጃዪ መንግሥት በናይጄሪያውያን የተተዉ የንግድ ተቋማትን እና ንብረቶችን መመዝገብ ጀምሯል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ከ600 በላይ ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት ወደ አገራቸው የሄዱ ሰዎች በአገሪቱ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ ይኖሩ የነበሩ ናቸው ቢሉም ናይጄሪያ ግን ነገሩን አስተባብላለች።

አንዳንድ ስደተኞችን የሚቃወሙ ቡድኖች ሕገ ወጥ የውጭ አገር ዜጎችን የሚቃወሙ ሰልፎች በቀጣይ ሳምንታት እንደሚቀጥሉ የተናገሩ ሲሆን፥ ማክሰኞ ዕለትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ሰልፍ ተደርጎ ነበር።

ሰልፎቹ በአብዛኛው ሰላማዊ የነበሩ ቢሆንም በውጭ አገር ዜጎች ላይ የተነጣጠሩ የተናጠል የጥቃት ክስተቶች ታይተዋል ሲል ቢቢሲ አክሎ አስነብቧል።

ሀናን ሽምሱ

ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *