የምክር ቤት አባላት በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የፋይናንስና የቤት ልማት ስትራቴጂው እንዲቀናጅ ጠየቁ

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ በጀት ላይ ማብራሪያ እየሰጡ ባሉበት በዚህ መድረክ፤ በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግር መፍታት የሚያስችል የተቀናጀ ስትራቴጂ እንዲዘረጋ የምክር ቤት አባላት ጠንካራ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ በጥያቄያቸው፤ በከተሞች እየታየ ያለውን ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ተከትሎ የቤት ፍላጎቱና ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍም የቤት ልማት ሥራዎችን፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን እና የፋይናንስ ተቋማትን አቅም የሚያስተባብር ግልጽና የተቀናጀ ስትራቴጂ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በተለይም በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ለሚኖሩ ዜጎች የሚመጥኑ የቤት አቅርቦት አማራጮችን በግልጽ ማስቀመጥ እንደሚገባና ባንኮችን ጨምሮ የፋይናንስ ተቋማት በቤት ልማት ዘርፍ ላይ ያላቸው ሚና እና ተሳትፎ ሊጎለብት እንደሚገባው የምክር ቤቱ አባላት በጥያቄያቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከተሞች ማደግና መለወጥ ያለባቸው ከዜጎች የመኖሪያ ቤት ዋስትና ጥያቄ ጋር በተቀናጀ መልኩ መሆን እንዳለበትም ተመልክቷል፡፡

ልዑል ወልዴ

ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *