የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2019 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
በዚህም መሰረት 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የፌደራል መንግስት የ2019 በጀት ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የፀደቀው ጠቅላላ በጀት ከ2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ411 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወይም 21 ነጥብ 3 በመቶ እድገት እንዳለው ተገልጻል፡፤
ሰኔ 30/2018 ዓ.ም
