ጋና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሊያደርጉት ያሰቡትን ይፋዊ የሀገር ጉብኝት ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ ተገለጠ


የጋና ባለስልጣናት ለዲደብሊው (DW) እንደተናገሩት፤ ሀገሪቱ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሊያደርጉት ያሰቡትን ይፋዊ የሀገር ጉብኝት ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች።
 
ይህ ውሳኔ የተሰማው በደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ከተቀሰቀሰው የውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ጋር ተያይዞ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት በከረረበት ወቅት ነው።
 
ከጋና መንግስት የተገኙ ምንጮች እንደገለጹት፤ በነሐሴ መጀመሪያ ላይ ይደረጋል ተብሎ ታስቦ የነበረው ይፋዊ ጉብኝት ውድቅ የተደረገው፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የህዝብ ስሜት ገና ባልበረደበት በአሁኑ ወቅት በጋና ውስጥ ሊነሳ የሚችለውን የህዝብ ተቃውሞ እና ቁጣ ለማስቀረት ሲባል ነው።
 
የጋና ባለስልጣናት የዜጎቻቸው ደህንነት እና ክብር ሁልጊዜም ቀዳሚ ተግባራቸው መሆኑን ገልጸዋል።
 
አክራ (የጋና መዲና) ማንኛውም ከፍተኛ የባለስልጣናት ጉብኝት ከመደረጉ በፊት፤ ፕሪቶሪያ ጥቃቶቹን ለማስቀረት እና የውጭ ሀገራት ዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንድትወስድ ማሳሰቧም ተነግሯል።
 
ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *