የቻይና ቀስ በቀስ እየጨመረ የመጣው የጫና ስልት በታይዋን የባህር ሰርጥ ላይ አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የመፍጠር ስጋት እንዳለው የታይዋን የውቅያኖስ ጉዳዮች ምክር ቤት ኃላፊ ገልጸዋል፡፡
ባለስልጣኗ በታይፔ በተካሄደ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ቻይና በባህር ላይ በምታደርገው እንቅስቃሴ ታይዋንን ብቻ ሳይሆን ጃፓንና ፊሊፒንስንም ጭምር እየተጫነች ነው።
የእነዚህ እንቅስቃሴዎች ትልቁ አደጋ፣ ጫናዎቹ ቀስ በቀስ ስለሚጨምሩ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሳይረዳው ነገሮች ከረፈዱ በኋላ ሊገለጥ መቻሉ ነው ብለዋል።
“እያንዳንዱ ግለሰባዊ ድርጊት ዓለም አቀፍ ቀውስ የሚቀሰቅስ ላይመስል ይችላል ነገር ግን ተከታታይ እርምጃዎች ሲከማቹ ሙሉ በሙሉ አዲስ ነባራዊ ሁኔታን ሊፈጥሩ ይችላሉ” ስትል ኩዋን አስገንዝባለች።
ታይዋንን የራሷ ግዛት አድርጋ የምትመለከተው ቻይና በየቀኑ ወታደራዊ ኃይሏን ወደ ደሴቲቱ የአየር ክልል ከመላክ ባለፈ፣ በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ መደበኛ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ቁጥጥር በማድረግ ላይ ትገኛለች።
የቻይና የታይዋን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ለቀረበለት የአስተያየት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።
ቤጂንግ ለውጥረቱ ታይዋንን የምትወቅስ ሲሆን፤ በተለይም ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ-ቴንን ‹‹ገንጣይ››ስትል ትጠራቸዋለች።
በተጨማሪም ባለፈው ወር አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን በቻይና አዲስ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ላይ ስጋታቸውን መግለፃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሳራ ዮሐንስ
ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም
