MSI ኢትዮጵያ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ21 ሚሊዮን ብር የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ

ድጋፉ በዋናነት በ220 የጤና ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ከ840 በላይ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎቱን እንዲያቀላጥፉ ታስቦ የቀረበ ነው።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤም ኤስ አይ  ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ እንደገለፁት የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ለማጠናከር የሚረዱ የ21 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶችን ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስረክበናል ብለዋል።

ቁሳቁሶቹ በዋናነት ለረጅም ጊዜ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የሚውሉና ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚረዱ መሆናቸው ተገልጿል።

ድርጅቱ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለጤና ተቋማት ማሰራጨቱን አስታውቋል።

ከቁሳቁስ ድጋፉ በተጨማሪ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ለመቅረፍ ከጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ዶክተር አበበ  ገልጸዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *