በደሞስተኛው ላይ የተጣለው የግብር መጠን ሊሻሻል እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የደሞስተኛው ማህበረሰብ ከከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚደርስበትን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ፣ መንግስት በደሞዝ ላይ የጣለውን የግብር መጠን  ሊያሻሽል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የፕራግማ ካፒታል መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መርዕድ ፍቅረ ዮሐንስ ፤ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በደሞስተኛው ላይ ከፍተኛ የግብር መጠን የምትጥል ሀገር በመሆኗ ይህ አሰራር ሊፈተሽ እንደሚገባ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በደሞስተኛው ላይ የተጣለው የታክስ መጠን በከተሞች ውስጥ ካለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት አንጻር ኑሮን እጅግ አዳጋች እንዳደረገው አንስተዋል፡፡

​በሀገሪቱ እየታየ ያለውም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 14 በመቶ ዝቅ ማለቱ ቢነገርም፣ አሁንም በተግባር ያለው የኑሮ ውድነት ጫና ግን በደሞስተኛው ማህበረሰብ ላይ ያለው ተጽዕኖ እጅግ የበረታ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል፡፡  

እንዲሁም  የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቀላሉ ሊቋቋመው የማይችለው ከውጭ የሚገባ የዋጋ ግሽበት መኖሩ በሀገር ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ይበልጥ እያባባሰው እንደሚገኝ አቶ መርዕድ ጠቅሰዋል፡፡

​መንግስት በበኩሉ ይህንን እየተስተዋለ ያለውን የኢኮኖሚ መዋዠቅና የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር፣ እንደ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ያሉ የተለያዩ የኢኮኖሚ ማረጋጊያ አሰራሮችን በተግባር ላይ እያዋለ ይገኛል ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

ሰላማዊት ዲታ

ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *