ናይጄሪያ እና ጋና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አፍሪካውያንን ኢላማ ያደረጉ የቅርብ ጊዜ ‹‹አፍሮፎቢክ ተቃውሞዎችን›› አውግዘዋል።
የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ሁለቱ ሀገራት ጉዳዩ በሚቀጥለው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አጀንዳ ላይ እንዲካተት እንደሚፈልጉ ገልጿል።
የናይጄሪያ እና የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በላይቤሪያ በተካሄደው የኢኮዋስ ስብሰባ ጎን ለጎን ውይይት አድርገዋል።
ደቡብ አፍሪካ ባላት አንጻራዊ ብልጽግና ምክንያት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ስደተኞችን ለረጅም ጊዜ ስትስብ የቆየች ሲሆን፣ ይህም አልፎ አልፎ ለሚከሰቱ ውጥረቶች መንስኤ ሆኖ ቆይቷል።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እየጨመረ በመጣው የሌላ አገር ሰዎች ጥላቻ ተቃውሞ እና ጥቃት ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች ከሀገሪቱ ሸሽተዋል።
ፀረ-ስደተኛ ቡድኖች ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ‹‹የጊዜ ገደብ›› ካስቀመጡ በኋላ፣ ወደ 1ሺህ5መቶ የሚጠጉ ናይጄሪያውያን እና ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ጋናውያን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
አቡጃ እና አክራ ተቃውሞዎቹ የአፍሪካ ህብረት የሚወክላቸውን የአፍሪካ አንድነት፣ ትብብር እና ቀጣናዊ ውህደት እሴቶችን የሚጎዱ ናቸው ብለዋል።
ሀገራቱ አስቸኳይ የተቀናጀ ቀጣናዊ ምላሽ እንዲሰጥ እና በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ክትትልን፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን እና የመከላከያ ዲፕሎማሲን ጨምሮ ጠንካራ አሰራሮች እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ የተባረሩ ዜጎቿ ጥለውት ለወጡት ንብረት እና ንግድ ከደቡብ አፍሪካ ካሳ እንደምትጠይቅ አስታውቃለች።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም
