ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በዛሬው ዕለት የመገናኛ ብዙኃን ባለድርሻ አካላትን በመጥራት ባዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩን አካሂዷል ፡፡
የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ”ተስፋን እንተክላለን” በሚል መሪ ቃል የባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀበና ወንዝ ዳርቻ በጋራ አከናውኗል፡፡
በዕለቱም ክብርት ሃይማኖት ዘለቀ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች አንዱ የሆነውን ይኸው ተግባር በየዓመቱ የሚያከናውነው ነው፡፡
በዕለቱም ክብርት ሃይማኖት ዘለቀ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ችግኝ በመትከል ሁሉም ሰው ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
