ዩናይትድ ስቴትስ «የግዴታ የጉልበት ብዝበዛ የተካሄደባቸውን ምርቶች ለማገድ በቂ እርምጃ አልወሰዱም» ባለቻቸው 60 አገራት ላይ ከ10 እስከ 12 ነጥብ 5 በመቶ የሚደርስ አዲስ የንግድ ታሪፍ ጥላለች።
ከአርብ ጀምሮ ስራ ላይ የሚውለው ይህ አዲስ ታሪፍ፤ ብሪታንያ፣ ቻይና፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ካናዳ፣ ጃፓን እና ህንድን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ ዋና ዋና የንግድ አጋሮችን ያካተተ ነው ይላል የቢቢሲ ዘገባ።
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር እንደሚለው፤ የጉልበት ብዝበዛን ለመግታት ቃል የገቡ አገራት 10 በመቶ፣ የተቀሩት ደግሞ 12 ነጥብ 5 በመቶ ታሪፍ ይጣልባቸዋል።
የአሜሪካ የንግድ እንደራሴ ጄሚሰን ግሪር በሰጡት መግለጫ፤ ውሳኔው «የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለማረም እና የሰራተኞችን ደህንነት ለማሻሻል ያለመ ነው» ብለዋል።
ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም
«አሜሪካ በ60 አገራት ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ ጣለች።»
