ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ወታደራዊ ላልሆነ አገልግሎት የሚውለው ይህ የኒውክሌር ስምምነት የሚጸድቀው ሳዑዲ አረቢያ የአብርሃም ስምምነቶችን ለመቀላቀል ስትስማማ ብቻ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል ሳዑዲ አረቢያ የፍልስጤም መንግሥት ሳይመሠረት ለእስራኤል ዕውቅና እንደማትሰጥ ገልጻ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን ለትራምፕ ቅድመ ሁኔታ የሰጠችው ምላሽ የለም።
በሌላ በኩል፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፣ ሳዑዲ አረቢያ ስምምነቱን ተቀብላ የእስራኤል ወዳጅ መሆኗ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምን ለማስፈን ትልቅ ታሪካዊ እርምጃ እንደሚሆን በመጥቀስ የትራምፕን ሃሳብ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም
አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ያደረጉት የሲቪል ኒውክሌር ስምምነት ይጸድቅ ዘንድ፤ ሪያድ ለእስራኤል ዕውቅና የሚሰጠውን የ‘አብርሃም አኮርድስ’ ስምምነት መቀላቀል እንዳለባት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ።
