ኢራን አድርጋው የነበረውን አጭር የተኩስ አቆም አቋርጣ በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ደጋፊ ኃይሎች ላይ ድንገተኛ የሚሳኤል ሰንዝራለች፡፡
የአሜሪካ መካከለኛው ዕዝ እንደገለጸው ጥቃቱ ማክሰኞ ዕለት የተፈጸመ ሲሆን፣ ሁሉም ሚሳኤሎች በስኬት መመከታቸውን አስታውቋል።
የአሜሪካ እና የሳዑዲ አረቢያ ኃይሎች ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ በኢራን ታጣቂዎች ከተፈጸሙ ከ30 በላይ የድሮን ጥቃቶች በኋላ በኢራቅ የሚገኙ የኢራን ደጋፊ ታጣቂዎች ላይ ድብደባ ፈጸመዋል። ከአስር በላይ ሰዎችም ሞተዋል ተብሏል፡፡
ሳዑዲ አረቢያ በሀገሪቱ የምስራቃዊ ክፍሎች በሚገኙ የነዳጅ ማዕከላት ላይ ያነጣጠሩ ድሮኖችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች።
አሜሪካ ተጨማሪ ወታደራዊ ምላሽ ላለመስጠት የኢራን ሠራዊትና ተላላኪዎቹ ጥቃቶቻቸውን እንዲያቆሙ አሳስባለች ፎክስ ኒውስ እንደዘገበው።
በሌላ ዜና ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ 3 የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ማገዷ እና ሙሉ ቁጥጥሯንም አጠናክራ መቀጠሏ ተዘግቧል፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባሕር ኃይል እንዳስታወቀው፣ ማስጠንቀቂያዎችን ችላ ብለው ደህንነቱ ያልተጠበቀ እና ሕገ-ወጥ ነው ባለው መስመር መጓዛቸውን የቀጠሉ 3 የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ኢላማ በማድረግ ማስቆሙን ገልጿል።
“የአሜሪካን ጦር ሕገ-ወጥ ትዕዛዝ” የሚከተሉ መርከቦች የሚያስከትለውን መዘዝ ይጋፈጣሉ ሲል አብዮታዊ ዘቡ አስጠንቅቋል።
ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
