የአሜሪካ-ኢራን ግጭት ለበርካታ ቀናት ከቆየ አንጻራዊ ሰላም በኋላ ዳግም አገርሽቷል


አሜሪካ በወታደሮቿ ላይ የጥቃት ሙከራ ከተደረገ  በኋላ በኢራን ላይ “ከባድ” አጸፋ ሰነዘረች ፡፡

ለበርካታ ቀናትም፣ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ይገኛል በሚል ተስፋ ንግግሮች እንደገና በመጀመራቸው ሁለቱም ወገኖች ጥቃቶችን አቋርጠው ነበር። ትራምፕ ንግግሮቹን «እጅግ ወዳጃዊ ድርድሮች» ሲሉ ጠርተዋቸዋል፤ ምንም እንኳ ቴህራን ምንም ዓይነት ውይይቶች መደረጉን ብትክድም።
 
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል ማክሰኞ ዕለት በአሜሪካ ኃይሎች ላይ በተደረገው የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃት ሙከራ አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት በኢራን ላይ «ከባድ የጥቃት ማዕበል» አጠናቆ መውጣቱን አስታወቀ።
 
ሴንትኮም እንደገለጸው፤ የኢራን ጦር በዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮዎች እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ባሉ መርከቦች ላይ ለፈጸመው ተኩስ ምላሽ «ደርዘን የሚቆጠሩ» የእስልምና አብዮታዊ ዘበኞች ኃይል (IRGC) ኢላማዎችን መመታቱን ገልጿል።
 
የኢራን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ፤ የቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች በቁሽም ደሴት ላይ የሁለት ዓመት ሕፃንን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን ሕይወት የቀጠፉ ሲሆን፣ በሀገሪቱ ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ክፍሎች የሚገኙ ሌሎች አካባቢዎችም ተመተዋል።
 
ይህ የቅርብ ጊዜ ግጭት የጦርነቱን መባባስ ባሳየበት በዚህ ሳምንት የተከሰተ ሆኗል ፤ በይፋ የታወጀ የመጀመሪያው የአሜሪካ እና ሳውዲ ጥምር ጥቃት በኢራቅ የሚገኙ የኢራን ታጣቂ ወኪሎችን ኢላማ አድርጓል ያለው ቢቢሲ ነው ።
 
አሜሪካ እና እስራኤል በየካቲት ወር በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃቶችን በጀመሩበት ጊዜ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ የሚቆየው ለጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደሆነ ተናግረው ነበር፤ ነገር ግን ምንም የመፍትሔ አቅጣጫ ሳይታይለት ለ አምስት ወራት ቀጥሏል።
 
ረዕቡ ዕለት፣ አክሲዮስ የተባለው የዜና ማሰራጫ ተቋም ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለሥልጣንን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሳውዲ የመከላከያ ሚኒስትር ልዑል ኻሊድ ቢን ሰልማን ጋር ተገናኝተው እንደነበር፣ ሳውዲ አረቢያ ውጥረቱን ማብረድ እንደምትፈልግም ሚኒስትሩ ገልጸው ነበር።
 
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *