ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ባለፉት ስምንት ዓመታት በሕዝባዊ ቁርጠኝነትና በጋራ እሳቤ እየተመራ ይበልጥ እየጠነከረ መቀጠሉን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከኮፕ32 ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ ሂደቱን በማከናወን ዐሻራቸውን አሳርፈዋል።
ዛሬ የሚካሄደው ዓመታዊው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂ ሀገር የማስረከብ ዓላማ ያለው መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተቀመጠውን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ታላቅ ሀገራዊ ግብ ለማሳካት መላው ኢትዮጵያውያን ቀኑን ሙሉ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሐምሌ 27 /2018 ዓ.ም
“የተቀመጠውን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ግብ ለማሳካት መላው ኢትዮጵያውያን ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ”
