ግብፅ 5.5 መጠን በተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተገለጸ

ዛሬ ማለዳ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ላይ፣ ከግብፅ ሱዊዝ ከተማ በስተሰሜን 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የ5.5 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በካይሮ እና በአል-አሪሽ ከተሞች ጭምር ተሰምቷል ነዉ የተባለዉ።

ባለሥልጣናት እስካሁን የደረሰ የሰው ሕይወት መጥፋትም ሆነ ከፍተኛ የንብረት ውድመት እንዳልተመዘገበ ገልጸዋል።

ግብፅ ቀደም ሲል አውዳሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን ብታስተናግድም፤እንዲህ ያሉ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጦች በአገሪቱ ውስጥ በአንጻራዊ ሁኔታ ብዙም የተለመዱ አይደሉም።

በግብፅ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በጥቅምት 1992 ሲሆን፤ በወቅቱ በካይሮ አቅራቢያ የደረሰው የ5.8 መጠን የመሬት መንቀጥቀጥ ከ500 በላይ ሰዎችን መግደሉ፣ በሺዎች የሚቆጠሩትን ማቁሰሉ እና ብዙዎችን ቤት አልባ ማድረጉ ይታወሳል።

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *