በሀገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ እስካሁን ከ578 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ፤ በዛሬው መርሃ ግብር 18 ነጥብ 6 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው የተሳተፉ ሲሆን፣ በዚህም የታቀደውን 72 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
የተተከለው ችግኝም ከ209 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን ነው።
አክለውም፤ ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ከደለል ከመጠበቅ ባለፈ፣ የበጋ መስኖን በማጎልበት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ጠንካራ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
ዛሬ ማለዳ በጀመረው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር እስካሁን ከ578 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተከሉ።
