የብሪታንያ የባህር ላይ ደህንነት ኤጀንሲ በኦማን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ አንድ የጭነት መርከብ ‹‹ባልታወቀ ተወንጫፊ አካል››መመታቱን አስታውቋል።
አንድ የጭነት መርከብ በኦማን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ‹‹ባልታወቀ ተወንጫፊ አካል›› መመታቱን የብሪታንያ የባህር ላይ ኤጀንሲ ማክሰኞ ዕለት የገለጸ ሲሆን፤ ስለደረሰው ጉዳት ወይም ስለቆሰሉ ሰዎች ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ መርከብ ‹‹ባልታወቀ ተወንጫፊ አካል ተመትቻለሁ›› ሲል ሪፖርት ማድረጉንና ባለሥልጣናት ምርመራ እያደረጉ መሆኑን የዩናይትድ ኪንግደም ማሪታይም ትሬድ ኦፕሬሽንስ ገልጿል።
ኤጀንሲው አክሎም ድርጊቱ የተፈጸመው ከኦማኗ አል ካሳብ ከተማ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በስተሰሜን ምስራቅ መሆኑን አስታውቋል።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም
