25 የአሜሪካ ግዛቶች በትራምፕ አስተዳደር ላይ አጠቃላይ አዲስ የታሪፍ ግዴታዎችን በመቃወም ክስ መሰረቱ

ሃያ አምስት የአሜሪካ ግዛቶች ሰፊ የታሪፍ ደንቦችን በመቃወም በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ላይ ክስ መስረተዋል።

ግዛቶቹ ፕሬዝዳንቱ በደርዘን በሚቆጠሩ አገራት ላይ አዳዲስ ቀረጦችን በመጣላቸው ስልጣናቸውን ተላልፈዋል ሲሉ ይከራከራሉ።

ግዛቶቹ ክሱን በኒውዮርክ በሚገኘው የዩኤስ ዓለም አቀፍ የንግድ ፍርድ ቤት የመሰረቱ ሲሆን፤ዳኞች የታሪፎቹን አፈጻጸም እንዲያቆሙ፣ ህገ-ወጥ መሆናቸውን እንዲያውጁ እና መንግስት ተመላሽ ክፍያ እንዲፈጽም እንዲያዝ ጠይቀዋል።

የግዛቶቹ ጥምረት ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ፤ የዩኤስ የንግድ ተወካይ ቢሮን በመጥቀስ፣ ‹‹በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ውስጥ አለ በተባለው የግዳጅ የጉልበት ብዝበዛ ችግር እና በዩኤስ የንግድ ተወካይ ቢሮ በተጣለው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ታሪፍ መካከል ምንም ዓይነት ምክንያታዊ ግንኙነት የለም››ሲል ተከራክሯል።

ተቃውሞው ትራምፕ ባለፈው ወር በ60 የንግድ አጋሮች ላይ በጣሉትና አብዛኛውን የአሜሪካ ገቢ ምርቶች በሚሸፍኑት ከ10 እስከ 12.5 በመቶ የሚደርሱ አዳዲስ ታሪፎች ጋር የተያያዘ ነው።

ትራምፕ ለሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ኃላፊነት ከተረከቡ ጀምሮ፤በዋሽንግተን ወዳጆችም ሆኑ ጠላቶች ላይ አንዳንድ ጊዜ እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ሰፊ ታሪፎችን በመጣል የዓለምን ንግድ አናውጠዋል።

ዋይት ሃውስ በትራምፕ ታሪፎች ላይ ለቀረበው አዲስ ተቃውሞ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፤የመንግስት እርምጃ ህጋዊ ነው ሲል ተከራክሯል።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ኩሽ ዴሳይ በመግለጫቸው፤ ‹‹ዩናይትድ ስቴትስ የአሜሪካን ንግድ የሚያውኩ ኢ-ምክንያታዊ ድርጊቶች፣ ፖሊሲዎች እና አሰራሮች እንዲወገዱ ለማድረግ ህጋዊ ስልጣኗን እየተጠቀመች ነው››ብለዋል።

ሀና ሰይፉ

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *