በኢኮኖሚ አሻጥርና የኮንትሮባንድ ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ አካላት በሕግ መጠየቅ ጀመሩ

በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሂደት ላይ እንቅፋት ለመፍጠርና የሀገር ሀብት ለመዝረፍ በተንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ሰፊ የሕግ ማስከበር እርምጃ መወሰዱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
 
አገልግሎቱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ እርምጃው በፋይናንስ፣ ንግድ፣ ነዳጅ፣ ማዕድን፣ ገቢዎችና ጉምሩክ፣ ቤቲንግና ፊንቴክ፣ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዘርፎች የተፈጸሙ የሙስና፣ የኮንትሮባንድ እና የሕገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ወንጀሎችን መሠረት ያደረገ ነው።
 
ከታገዱና እርምጃ የተወሰደባቸው አካላት መካከል ከ7,000 በላይ ድርጅቶችና መጋዘኖች ታሽገዋል፡፡169 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለዋል ፤183 ግለሰቦች በወንጀል ተጠያቂ ሆነዋል ፡፡ከ650 በላይ በሚሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተብሏል ፡፡እንዲሁም 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርገዋል፡፡
 
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ መንግሥት ሌብነትና ሕገ-ወጥ አሠራሮችን የመዋጋት እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ሕዝቡም ሕገ-ወጦችን በማጋለጥ ረገድ ከጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
 
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *