የአፍሪካ ህብረት በሱዳን የጀመረውን የሰላም ተልዕኮ ስኬታማ ለማድረግ የጦር ሜዳ እና የዲፕሎማሲ መሰናክሎችን መጋፈጥ ግድ ይለዋል ተባለ

ባለፉት ሶስት አመታት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት የዳረገውን እና በሚሊየኖች የሚቆጠሩትን ያፈናቀለውን አስከፊ ጦርነት ለማቆም የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ልዑክ በሱዳን የሁለት ቀናት የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ተልዕኮው በሱዳን መደበኛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ፤የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማሻሻል እና ሁሉንም ያካተተ የፖለቲካ ሂደትን እንደገና ለማንቀሳቀስ ያለመ ነው።

ነገር ግን ይህ ተልዕኮ የተጀመረው ጦርነቱ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በደረሰበት ወቅት ነው።

የሱዳን መደበኛ ጦር የዋና ከተማዋን ካርቱም አብዛኛውን ክፍል መልሶ በመቆጣጠር ረገድ ወታደራዊ ሚዛኑን ቢያስተካክልም፤ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ደግሞ በምዕራብ ሱዳን በዳርፉር ሰፊ ግዛቶች ላይ መሽገው ይገኛሉ።

የትኛውም ወገን ወሳኝ ድል ማግኘት ባይችልም፤ ሁለቱም ኃይሎች በጦር ሜዳ የሚያገኟቸው ጊዜያዊ ድሎች በድርድር ጠረጴዛው ላይ የተሻለ ተሰሚነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በማመን ውጊያውን ቀጥለዋል።

አገራዊ የተኩስ አቁም ከመፈለግ ይልቅ የሲቪል ማህበረሰቡን በሰላም ሂደቱ ውስጥ በይፋ ማካተት እና በአፍሪካ የሚመራ የክትትል ስርዓት በመሬት ላይ መዘርጋት እንዳለበት የፖለቲካ ተንታኞች ያሳስባሉ።

ሳራ ዮሐንስ

ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *