በደቡባዊ ፔሩ የአንዲስ ተራሮች አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲቆስሉ የነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶች፣ የጤና ጣቢያዎች እና ትምህርት ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
እንደ አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ፤የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በባያኮቾ ክልል ፓሪናኮቻስ ግዛት ከሚገኘው ኡፓሁዋቾ ከተማ በሰሜን ምዕራብ 38 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲሆን፥ጥልቀቱም 66 ኪሎ ሜትር እንደነበር ተገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በደቡባዊ ፔሩ በሚገኙ በርካታ ክልሎች ኢካ፣ አሬኪፓ፣ ሁዋንካቬሊካ፣ አፑሪማክ እና ኩስኮ፣ እንዲሁም በዋና ከተማዋ ሊማ ሳይቀር መሰማቱን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
የሲቪል መከላከያ ኃላፊው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፥ በፓሪናኮቻስ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ኮራኮራ የመሬት መንቀጥቀጡ በተከሰተበት ወቅት ከመኖሪያ ቤታቸው ለማምለጥ የሞክሩ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ኃላፊው አክለውም በኮራኮራ አቅራቢያ የድንጋይ መደርመስ አደጋዎች መከሰታቸውን ገልጸው፥ የፔሩ የባሕር ኃይል የሱናሚ አደጋ ሥጋት አለመኖሩን አረጋግጧል ብለዋል።
እድላዊት ብርሃኑ
ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም
