አሜሪካ የኢራንን አገዛዝ “የሚያፈርሱ” ማዕቀቦችን እንደምትጥል ዛተች

አሜሪካ የኢራንን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ለማዳከም እና አገዛዙን ለመለወጥ የሚያስችሉ ከባድ ማዕቀፎችን እና አዲስ የኢኮኖሚ ጦርነት እቅድ ይፋ ማድረጓን አስታወቀች።
 
ኢራን ይህንን ዘመቻ ዋሽንግተን ላይ “ተጨማሪ ሽንፈት” የሚያስከትል ስትል አጣጥለዋለች፡፡
 
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሰንት፤ አገራቸው በኢራን ላይ ልትወስድ ያሰበችው እርምጃ “በዓለም ታሪክ ውስጥ ትልቁ የተቀናጀ ኢኮኖሚያዊ የማግለል” ዘመቻ አካል መሆኑን ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ከኢራን ጋር የንግድ ግንኙነት የሚፈጽሙ፣ ገንዘብ የሚያዘዋውሩ ወይም ነዳጅ የሚገዙ ማናቸውም አገራት ላይ ጠንካራ የአሜሪካ ማዕቀፍ እንደሚጣል አስጠንቅቀዋል።
 
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቴህራን ላይ የከፈተው የኢኮኖሚ ጦርነት በአሜሪካ ላይ ተጨማሪ ሽንፈት የሚያስከትል እና ዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ላይ አደጋ የሚደቅን “ኢኮኖሚያዊ ሽብርተኝነት” ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
 
አራግቺ በኤክስ ገጻቸው ላይ ” ‘የኢኮኖሚ ጦርነት’ የሚባለው ከአሜሪካ ቀውስ ትኩረትን ለማስቀየር” የተወሰደ እንደሆነ በመግለፅ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ 40 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን ከቀውሶቹ አንዱ አድርገው ጠቅሰዋል።
 
ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *