በኔፓል በበረዶ ግግር መደርመስ ምክንያት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ8መቶ በላይ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተገለጸ፡፡

በኔፓል እና ቲቤት ድንበር አካባቢ በተከሰተው በዚህ አደጋ፣ ከፍተኛ የሆነ የጭቃ እና የውሃ ማዕበል መኖሪያ ቤቶችን ደምስሷል፤ መንገዶችን እና ድልድዮችንም ጠራርጎ ወስዷል።

በአሁኑ ወቅት የህይወት አድን ቡድኖች የተረፉ ሰዎችን ለማፈላለግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃ በኔፓል ከ8መቶ በላይ ሰዎች የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን፤ የ1መቶ77 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።

ሆኖም በአካባቢው ላይ እየዘነበ ባለው ሀይለኛ ዝናብ እና የአካባቢው አስቸጋሪ መልክአ-ምድር ምክንያት የፍለጋ ስራው ፈታኝ ሆኗል።

በቲቤት በኩል ደግሞ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፤ የ5መቶ58 ሰዎች ደብዛ ጠፍቷል።

እስካሁን ድረስ በሁለቱም ድንበሮች በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ያሉበት አልታወቀም።

የኔፓል ባለስልጣናት እንዳሳወቁት ከሆነ ከጠፉት መካከል 1መቶ78 የህንድ፣ 1መቶ27 የኔፓል፣ 65 የአሜሪካ፣ 35 የአውስትራሊያ እና 33 የብሪታንያ ቱሪስቶች ይገኙበታል።

ሀና ሰይፉ

ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *