የቻይናው ፕሬዝዳንት በሚቀጥለው ወር ወደ ዋሽንግተን ለሚያደርጉት ጉብኝት ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ዋሽንግተን እና ቤጂንግ በዢ ጂንፒንግ እና በዶናልድ ትራምፕ መካከል የተደረሱ ስምምነቶችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቻይና እና አሜሪካ ለከፍተኛ ደረጃ ልውውጦች እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለማሸነፍ በጋራ መስራት እንዳለባቸው የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
ዢንዋ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ቤጂንግ እና ዋሽንግተን በሁለቱ ሀገራት መሪዎች የተደረሰውን ወሳኝ መግባባት በተግባር ማዋል እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚደረጉ ከፍተኛ ደረጃ ልውውጦች የሚፈጠሩ መስተጓጎሎችን እና እንቅፋቶችን ማስወገድ አለባቸው።
ሚኒስትሩ ይህንን አስተያየት የሰጡት በቤጂንግ ከአሜሪካው አምባሳደር ዴቪድ ፐርዱ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው።
የአሜሪካው አምባሳደር ባወጡት አጭር መግለጫ መሠረት፤ ሁለቱ ወገኖች ፕሬዝዳንት ዢ ወደ ዋሽንግተን ለሚያደርጉት የጋራ ጉብኝት ዝግጅት ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
ሳራ ዮሐንስ
ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም
