የኖርዌዩ ንጉሥ ሃራልድ አምስተኛ አልፎ አልፎ በሚከሰት የደም ሕመም ምክንያት ባለፈው ሳምንት በሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ በዛሬው ዕለት በ89 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የኦስሎ ቤተ መንግሥት እንደገለጸው፤ ንጉሡ አርብ ዕለት በኦስሎ ብሔራዊ ሆስፒታል በአካባቢው አቆጣጠር ከጠዋቱ 06:35 ላይ ህይወታቸው አልፏል።
ከዜናው መስማት ጋር ተያይዞ በቤተ መንግሥቱ ጣሪያ ላይ የሚገኘው የንጉሣዊው ቤተሰብ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲወለበለብ ተደርጓል።
ንጉሥ ሃራልድ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ በኖርዌይ ምድር የተወለዱ የመጀመሪያው የኖርዌይ ንጉሥ ነበሩ።
አሁን ላይ በልጃቸው ልዑል ዙፋን አልጋ ወራሽ ሀኮን ተተክተዋል።
ንጉሱ ለ35 ዓመታት በዙፋን ላይ በቆዩበት ዘመናቸው የቀደመውን ልማድ በመጣስ፤ ንጉሣዊ ሥርዓቱን በማዘመን፣ ከንጉሳዊ የዘር ግንድ ውጪ በማግባት እንዲሁም በኖርዌይ ፈታኝ ወቅት ሀገርን በማስተባበር ተወዳጅና ዘመናዊ መሪ በመሆናን ይታወሳሉ።
የንጉሣዊ ቤተሰቡ የቅርብ ሰዎች ንጉሡ ትሑት፣ የተከበሩና የተወደዱ እንደነበሩ በመግለጽ ‹‹የሕዝብ ንጉሥ›› እና የሀገሪቱ ‹‹አያት›› ሲሉ ይጠሯቸዋል፤ ይህም መጠሪያ ከአባታቸው ንጉሥ ኦላቭ አምስተኛ ጋር የሚጋሩት ነው።
ሀና ሰይፉ
ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም
