ተቋሙ በበጀት አመቱ 39.5 ቢሊየን የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡም ነዉ የተገለጸው።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት፤ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 4መቶ75.57 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያገኘ ሲሆን፤ ይህም ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ገቢውን ባለፉት ሦስት ዓመታት በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ በ2018 በጀት ዓመት 1መቶ24 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ችሏል።
ከተጠቀመበት 1መቶ52 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ወጪ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነውን በራሱ ገቢ መሸፈን መቻሉም ተገልጿል።
በኃይል ማመንጨት ዘርፍ የአሰላ 100 ሜጋ ዋት እና የአይሻ 80 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ኦፕሬሽን በመግባታቸው አጠቃላይ የማመንጨት አቅሙ በ23 በመቶ አድጓል።
በኃይል ስርጭትና ገቢ አሰባሰብ ረገድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 56.4 በመቶ ኃይል በመውሰድ ዋና የሀገር ውስጥ ተጠቃሚ ቢሆንም፤ 32.5 በመቶ የኃይል አቅርቦት ያገኘው የዳታ ማይኒንግ ዘርፍ 50.4 ቢሊየን ብር ገቢ በማስገኘት ከፍተኛውን የገቢ ድርሻ ይዟል።
በውጭ ሀገር ኤክስፖርት በኩል ደግሞ ለኬንያ 16 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለጅቡቲ 5.5 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጡ ተጠቅሷል።
ለዓለም አሰፋ
ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም
