የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት አብዛኛው የሩሲያ ማህበረሰብ ጦርነቱ አሁን እንዲቆም ይስማማል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንደተናገሩት፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሁለቱ ሀገራት መካከል አምስተኛ ዓመቱን የያዘውን ጦርነት ለመቀጠል ‹‹በግላቸው›› ፍላጎት አላቸው።
ዘለንስኪ ባስተላለፉት መልዕክት፤አብዛኛው የፑቲን የገዛ ማህበረሰብ ጦርነቱ አሁን ላይ እንዲቆም እንደሚስማማ ገልጸዋል።
ለጊዜው ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የእኛም ሆነ የአጋሮቻችን መረጃዎች እንዲሁም ከሩሲያ የሚመጡ ምልክቶች ሁሉ እንደሚያመለክቱት የሩሲያው መሪ በግላቸው ተጨማሪ ጦርነት ይፈልጋሉ ብለዋል።
ዘለንስኪ አክለውም ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች ከሆኑት ጃሬድ ኩሽነር ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።
ውይይቱም ከሩሲያ ወገን ጋር ስለሚደረግ ስብሰባ እና ተጨማሪ ግንኙነት ዝግጅት፤ እንዲሁም ወደ ዩክሬን ሊያደርጉት ስለሚችሉት ጉብኝት የሚመለከት ነበር።
ሩሲያ ጦርነቱን ወደ ማቆም እንድትመጣ ምን መደረግ እንዳለበት ተወያይተናል ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተወካዮች ምን ማሳካት እንደሚችሉ እናያለን። መስከረም ወር ብዙ ነገሮችን ሊለውጥ ይችላል ሲሉ አክለዋል።
እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
