አንድ የታይዋን ዜጋ የባለቤቱን ሌላ የፍቅር ግንኙነት በሮቦት የቤት ማፅጃ ካሜራ አማካኝነት ያለፍቃዷ ቀርፆ በመያዙ በአምስት ወር የእስራት ፍርድ እና በ150,000 የታይዋን ዶላር መቀጮ ተቀጥቷል።
ግለሰቡ በ2023 በሁለተኛ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተፈጠረ ጥርጣሬ ተነሳስቶ፣ በሞባይል መተግበሪያ የቤቱን ሮቦት ማፅጃ በርቀት በማስነሳት ባለቤቱ ከሌላ ወንድ ጋር ሆና በካሜራ ይዟታል።
ባል ምስሉን ለቀጣይ የሕግ ክስ እንደ ማስረጃ ለመጠቀም በማሰብ መቅረፁን የቀጠለ ሲሆን፣ በቪዲዮው ታግዞም ለደረሰበት የሞራል ጉዳት ከባለቤቱና ከፍቅር አጋሯ 500,000 የታይዋን ዶላር ካሳ አግኝቷል።
ሆኖም ግን፣ ስኬቱ ባለቤቱ ባቀረበችበት የመልስ ክስ ምክንያት ጥላ ያረፈበት ሆኗል።
በሮቦት ማፅጃው የተቀረፀው የቪዲዮ ማስረጃ የባለቤቱን አለመታመን ያረጋገጠ ቢሆንም፣ ሁለቱን ፍቅረኞች ያለፍቃዳቸው መቅረፁንም አረጋግጧል።
ባል ድርጊቱ ተገቢ እንደነበር ቢከራከርም፣ ፍርድ ቤቱ ግን የጋብቻ ግዴታዎች የሰዎችን የግል ሕይወት የመጠበቅ መብት አያልፉም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
በዚህም መሠረት በታይዋን ሕግ የሰዎችን የግል እንቅስቃሴ ያለፍቃዳቸው መቅረፅ ወንጀል በመሆኑ፣ ባል የካሳ አሸናፊ ቢሆንም በወንጀሉ ምክንያት የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ፍርድ ተፈርዶበታል።
ሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
